
ታማኝ የአጥንት
ሕክምና አጋርዎ!
3 አዲስ ኦርቶን
የሚመርጡበት ምክንያቶች

ከጅምር እስከ ፉፃሜ አገልግሎት
ከቅድመ-ሽያጭ እስከ ድህረ ሽያጭ ለደንበኞች ግላዊ ድጋፍ ለመስጠት ከአምራቾች ጋር በቀጥታ እንሰራለን።

ጥራት
ከታወቁ አምራቾች ጋር በመስራት ጥብቅ ሙከራዎችን እና ምርመራዎችን በማድረግ ጥራቱን እናረጋግጣለን።

ተመጣጣኝ ዋጋ
በቀጥታ ከአምራቾች ጋር እንነጋገራለን ፤ በዚህም መሰረት ለደንበኞቻችን አላስፈላጊ ወጪን እንቀንሳለን።
ስለ እኛ
አዲስ ኦርቶ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የአጥንት ህክምና መሳሪያዎች እና የቴክኒክ ድጋፍ የሚያቀርብ ኩባንያ ነው። በፌሎውሺፕ የሰለጠኑ የመገጣጠሚያ ቅየራ እና የአጥንት አደጋ ቀዶ ህክምና ሰብ-ስፔሻሊስት በሆኑት በዶ/ር ሳሙኤል ኃይሉ የሚመራው ኩባንያችን በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ ቀዶ ሐኪሞች እና ሆስፒታሎች የመገጣጠሚያ መቀየሪያ እና የአጥንት ስብራት መጠገኛ መሳሪያዎችን እና የቴክኒክ ድጋፍ ለማቅረብ ቁርጠኛ ነው። የኩባንያው የአሁኑ የአቅርቦት ትኩረት የዳሌ እና የጉልበት መገጣጠሚያ ቅየራ፣ የአጥንት አደጋ እና የዕጢ መልሶ ግንባታ እንዲሁም የአከርካሪ አጥንት መጠገኛ መሳሪያዎች ናቸው።
ራዕይ
አስተማማኝ የአጥንት ህክምና መሳሪያዎች እና የቴክኒክ ድጋፍ አቅራቢ መሆን።

የደንበኛ እርካታ
ቅድሚያ የምንሰጠው በአገልግሎታችን እና ከታካሚዎች ለሚመጡት ጥያቄዎች በምንሰጠዉ ፈጣን ምላሽ የደንበኞቻችንን እርካታ መጠበቅ ነው።

ትምህርት እና እርዳታ
ደንበኞቻችን ትክክለኛውን ምርት አና አገልግሎት እንዲያገኙ ትምህርት ስልጠና እና ድጋፍ እንሰጣለን።

ፈጠራ
በጥናት ላይ የተመሰረቱ ልዩ ምርቶቻችን እንዲሁም ከአምራቾች ጋር ያለን ቀጥተኛ ትብብር ልዩ ያደርገናል።
ተልዕኮ
ጥራት ያለው የአጥንት ህክምና አቅርቦቶችን እና አገልግሎቶችን ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ተደራሽ ማድረግ።

ጥራት ያላው አቅርቦት እና አገልግሎት
ተልዕኳችን ኢኮኖሚያዊ ደረጃቸውን ባገናዘበ መልኩ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን በተመጣጣኝ ዋጋ ከፍተኛ ጥራት ያለው የአጥንት ህክምና አቅርቦቶችን እና አገልግሎቶችን መስጠት ነዉ፡፡ድርጅታችን ጥራት ያለው የጤና እንክብካቤ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን በሀገሪቱ ውስጥ ያለዉን ክፍተት ለመሙላት ቁርጠኛ አላማ አለዉ።
አቅርቦቶቻችን




ምርቶቻችን የሚያገለግሉባቸው ቀዶ ህክምናዎች


\




\
የኩባንያችን የአጥንት ህክምና ሰብ-ስፔሻሊስት ቡድን
ዶ/ር ሳሙኤል ኃይሉ
የዳሌ እና ጉልበት መገጣጠሚያ ቅየራ እና
ከፍተኛ የአጥንት አደጋዎች ሰብ-ስፔሻሊስት

ዶ/ር ኤርሚያስ ግዛው
የአጥንት ካንሰረ ህክምና
ሰብ-ስፔሻሊስት

ዶ/ር ጌታሁን ገብረእግዚአብሔር
ከፍተኛ አጥንት ህክምና
ሰብ-ስፔሻሊስት

ዶ/ር ቢኒያም ተሾመ
ከፍተኛ አደጋዎች እና መገጣጠሚያ ቅየራ
ሰብ-ስፔሻሊስት

ዶ/ር ቃለአብ ተስፋዬ
አከርካሪ እና ከፍተኛ የአጥንት አደጋዎች
ሰብ-ስፔሻሊስት
የቅርብ ጦማሮች
-
In clinics and pharmacies across the country, a specific combination injection has become the ultimate go-to remedy. It’s locally known as “Diclo-Dexa”—a potent mix of Diclofenac and Dexamethasone. Whether it’s for severe gout, chronic back aches, sudden knee pain, or a general body ache, patients often request it by name. It is widely perceived as…
ያግኙን
ለክሊኒክ ቀጠሮ
የክሊኒክ ቀጠሮ፡ ቀጠሮ ይያዙ የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ወይም በመደወል በሳማሪታን ቀዶ ህክምና ማዕከል ከዶ/ር ሳሙኤል ኃይሉ ጋር ቀጠሮ ይያዙ።
ለድንገተኛ ህክምና፡ ያለቀጠሮ 24/7 በሳማሪታን ቀዶ ህክምና ማዕከል
አድራሻ፡-
በሳማሪታን ቀዶ ህክምና ማዕከል
ወሰን ሰንሻይን ሪል ስቴት ቤቶች የጀርባ በር፤
አሜሪካን ህክምና ማእከል አጠገብ
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ፡ +251-9 33 91 92 99
ቴሌግራም፡ t.me/DrSamuelHailu
ለምርቶቻችን
ምርቶቻችንን ለመግዛት
በአድራሻ ችን ይጠቀሙ ወይም ይደውሉ
አድራሻ፡-
የአዲስ ኦርቶ
ሳምዮን ህንፃ ከወሰን ሰንሻይን ሪል እስቴት ቤቶች ፊት ለፊት
የፖስታ ሳጥን ቁጥር 13198
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ፡ +251924 22 22 27 / 28
ቴሌግራም፡ t.me/AddisORTHO



