Specialist care

Orthopaedic services in Addis Ababa

Focused consultation pathways for joint replacement, complex trauma, hip preservation and related orthopaedic conditions.

አጠቃላይ የዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ

በትንሽ ጠባሳ፥ ጡንቻን ሳይቆረጥ እና በ ዳሌ ፊት ለፊት በኩል በሚደረግ የዳሌ ቅየራ በሀገራችን ፈር ቀዳጅ እንደመሆናችን በልዩነት ቀዶ ህክምናዉን እናደርጋለን።

አጠቃላይ የጉልበት ቅየራ

አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ እና በሀገረ አሜሪካ በሚመረቱ ሰዉ ሰራሽ የጉልበት መቀያየሪያዎችን በመጠቀም የጉልበት ቅየራ ህክምና እንሰጣለን።

ግማሽ የዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ

በፊት ለፊት በኩል በሚደረግ ቀዶ ህክምና ተደራራቢ ራስ ባለው አሜሪካ ሰራሽ መቀየሪያዎችን በመጠቀም የግማሽ ዳሌ ቅየራ ህክምና እናደርጋለን።

የዳሌ ራስ መበስበስ

በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያለ የዳሌ ራስ መበስበስ እንደ ኮር ዲኮምፕሬሽን ባሉ ዳሌን በሚያቆዩ ቀዶ ህክምናዎች ሊታከም ይችላል፤ ከ3 እስከ 5ኛ ደረጃ ላሉት ደግሞ ጡንቻ ሳይቆረጥ የሚደረግ ሙሉ የዳሌ ቅየራ ሊያስፈልግ ይችላል። አማራጮቹ በምክክር ወቅት ይታያሉ።

የዳሌ ገንዳ ስብራት

ለዳሌ ገንዳ ስብራቶችን የቀዶ ጥገና የጉዳት መጠን ዝቅተኛ በሆኑ ዘዴዎች የሚከሰተዉን ደም መፍሰስ በመቀነስ እና ቀዶ ህክምናዉን በአጭር ጊዜ እንድናከናዉን ይረዱናል።

የዳሌ ማቀፊያ ስብራት

ዶ/ር ሳሙኤል ኃይሉ በ2007 ዓ.ም በካናዳ ቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ አጥንት አደጋዎች የሰብ-ስፔሻሊቲ ፌሎውሺፕ ስልጠና ያጠናቀቁ ሲሆን የዳሌ ገንዳ እና የዳሌ ሶኬት (አሴታቡለም) ስብራቶችን በቀዶ ህክምና ያክማሉ።

የዳሌ ስብራት

ለዳሌ አጥንት ስብራት እንደአስፈላጉነቱ በትንሽ ጠባሳ በሚደረጉ፣ የጉዳታቸዉ መጠናቸው አነሰተኛ በሆኑ እና ጡንቻ በማይጎዱ ዘዴዎች ህክምና እናደርጋለን።

የዳሌ ስብራት

We provide hip fracture treatment, including percutaneous and minimal invasive fixations using cephalomedullary nails, dynamic hip screws, angle blade plates as deemed appropriate.

ብዙ ቦታ የሚከሰቱ ዉስብስብ ስብራቶች

ተለያዩ ዉስብስብ አጥንት ስብራቶችን ማለትም እንደ መገጣጠሚያ አካባቢ እና የተረከዝ ስብራቶች የጉዳት መጠናቸው አነስተኛ በሆኑ ዘዴዎች እናክማለን።

ክሊኒክ፦ ዶ/ር ሳሙኤል ኃይሉ በሳማሪታን ቀዶ ህክምና ማዕከል፣ ወሰን ሰንሻይን፣ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 13፣ አዲስ አበባ። ሰኞ፣ ረቡዕ እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 1:00 እስከ ቀኑ 8:00 ሰዓት (07:00–14:00)፣ በቀጠሮ።