Specialist team
Orthopaedic specialists in Addis Ababa
Meet surgeons with focused experience in joint replacement, orthopaedic oncology, spine and complex trauma care.

ዶ/ር ሳሙኤል ኃይሉ
በዳሌ እና ጉልበት መገጣጠሚያ ቅየራ
እና ከፍተኛ የአጥንት አደጋዎች ሰብ-ስፔሻሊስት
ዶ/ር ሳሙኤል የአጥንት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሲሆኑ፤ በዳሌ እና ጉልበት መገጣጠሚያ ቅየራ እንዲሁም ከፍተኛ አጥንት አደጋዎች ሰብ-ስፔሻሊስት ናቸው።
የዶ/ር ሳሙኤል የህክምና ልምድ እና ልዩ ትኩረት የሚያካትታቸው፡ -
* ከፊት ለፊት በኩል የሚደረግ የዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ፣
* የጉልበት ቅየራ
* የዳሌ ገንዳ ፣ የዳሌ ማቀፊያ & የዳሌ ስብራት ህክምናን ያከናውናሉ።
ዶ/ር ሳሙኤል የህክምና ዶክትሬት ድግሪ (ኤምዲ) በ2001 ዓ.ም፣ እንዲሁም የአጥንት ህክምና የስፔሻሊቲ ሰርተፍኬት በ2006 ዓ.ም ከ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምህርት ቤት ያገኙ ሲሆን፣ ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ በዚያው የማስተማር ሠራተኛ ናቸው። ከዚያም የአጥንት ስብራት እና የመገጣጠሚያ ቅየራ ንዑስ ስፔሻሊቲ ፌሎውሺፕን በሰንይብሩክ ሄልዝ ሳይንስ እና በሆላንድ ኦርቶፔዲክ እና አርትራይተስ ማዕከላት፣ በቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ፣ ካናዳ፣ በ2007 ዓ.ም አጠናቀዋል።
ዶ/ር ሳሙኤል ከፌሎውሺፕ በፊትም ሆነ በኋላ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሰርተዋል፤ ከ2008 እስከ 2016 ዓ.ም ደግሞ የአጥንት አደጋ (ትራውማ) ክፍሉን መርተዋል። የሥራ ትኩረታቸው የመገጣጠሚያ ቅየራ፣ የዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራን በፊት ለፊት አቀራረብ ማከናወንን ጨምሮ፣ እንዲሁም የዳሌ፣ የዳሌ ገንዳ እና የዳሌ መገጣጠሚያ ስብራት ህክምና ነው። የፊት ለፊት አቀራረብ ሊኖሩት ከሚችሉ ጥቅሞች መካከል አነስተኛ ጠባሳ እና አጭር የማገገሚያ ጊዜ ይገኙበታል፤ ጥቅሞቹ እና አደጋዎቹ በምክክር ወቅት ከእያንዳንዱ ታካሚ ጋር ይወያያሉ።
ዶ/ር ሳሙኤል የአጥንት ህክምና ተባባሪ ፕሮፌሰር ሲሆኑ፣ ለቀዶ ሐኪሞች እና ለሆስፒታሎች የመገጣጠሚያ መቀየሪያ እና የአጥንት ስብራት መጠገኛ መሳሪያዎችን እና የቴክኒክ ድጋፍ የሚያቀርበው የአዲስ ኦርቶ መስራችም ናቸው። የህክምና አገልግሎት የሚሰጡት በሳማሪታን ቀዶ ህክምና ማዕከልሲሆን፣ እዚያ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በትርፍ ጊዜ እያገለገሉ ነው። ሙሉ መገለጫ እና ጽሑፎች፡ drsamuelhailu.com.
ዶ/ር ኤርሚያስ ግዛው
Orthopedic Oncology Surgeon


ዶ/ር ቃለአብ ተስፋዬ
አከርካሪ መጣመም ሕክምና እና ከፍተኛ የአጥንት አደጋዎች ሰብ-ስፔሻሊስት
ዶ/ር ቃለአብ ተስፋዬ ከፍተኛ የአጥንት አደጋዎች እና የአከርካሪ አጥንት ቀዶ ጥገና ሐኪም ናቸው። የአዲስ ኦርቶ የቀዶ ጥገና ሐኪሞች ቡድን አባል ሲሆኑ በትርፍ ሰዓታቸው በኢትዮ-ኢስታንቡል አጠቃላይ ሆስፒታል ህክምና ይሰጣሉ።
የትምህርት ማህደር ፡-
- የዶክትሬት ዲግሪ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሕክምና ትምህርት ቤት በ2008 ዓ.ም
- በአጥንት ቀዶ ሕክምና ስፔሻልቲ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሕክምና ትምህርት ቤት በ2013 ዓ.ም
- የምስራቅ፣ የመካከለኛውና የደቡብ አፍሪካ ቀዶ ሕክምና ኮሌጅ (COSECSA) የ2013 ዓ.ም ምሩቅ
- የከፍተኛ የአጥንት አደጋ እና የአከርካሪ አጥንት ሕክምና ሰብ ስፔሻልቲ ከጋንጋ ሆስፒታሎች እና የህክምና ማእከላት ፣ ኮይምባቶር ህንድ በ2016 ዓ.ም
ዶ/ር ቃለአብ ለሁሉም ታካሚዎቻቸው ከፍተኛ ጥራት ያለው የአከርካሪ አጥንት አደጋ፣ የአከርካሪ አጥንት ኢንፌክሽኖችና ዕጢዎች፣ የዳሌ እና የዳሌ ማቀፊያ ስብራቶች እና ከፍተኛ አደጋዎች ሕክምናን ይሰጣሉ።
ህመምን ለመቀነስ እና አጭር የሆስፒታል ቆይታን ለማረጋገጥ እንዲሁም ታካሚዎች በፍጥነት አገግመው ወደ መደበኛ ጤናማ ህይወታቸው በቶሎ እንዲመለሱ የሚረዳውን ዘመኑ ያፈራቸው የምርመራ መሳሪያዎች እና የህመም ማስታገሻ ዘዴዎችን በመጠቀም ሕክምና ይሰጣሉ።
የአዲስ ኦርቶ የቀዶ ጥገና ሐኪሞች ቡድን አባል ሲሆኑ በኢትዮ-ኢስታንቡል አጠቃላይ ሆስፒታል ይገኛሉ።
ዶ/ር ቢኒያም ተሾመ
ከፍተኛ የአጥንት አደጋዎች እና መገጣጠሚያ ቅየራ
ሰብ-ስፔሻሊስት
ዶ/ር ቢኒያም ተሾመ የከፍተኛ የአጥንት አደጋዎች እና መገጣጠሚያ ቅየራ ሰብ-ስፔሻሊስት ናቸው። በውስብስብ የጡንቻ እና የአጥንት ስርዓት የቀዶ ሕክምና አስተዳደር ውስጥ ሰፊ ልምድ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ልምድን የያዙ ሐኪም ናቸው።
ከባህር ዳር ዩንቨርስቲ የህክምና ዶክትሬት ዲግሪያቸውን በተጨማሪም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የስፔሻሊቲ ስልጠናቸውን አጠናቀዋል። የCOSECSA ሰርተፍኬት ከሩዋንዳየያዙ ሲሆን በቀጣይም በእንግሊዝ በርሚንግሃም ዩኒቨርሲቲ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እና በኩዊን ኤልዛቤት ሆስፒታል የሰብ-ስፔሻሊቲ ስልጠናቸውን ተከታትለዋል። እንዲሁም በሆስፒታል '12 de Octubre በማድሪድ' ፣ ስፔንየሕክምና ጥናታቸውን አጠናቀዋል።
ዶ/ር ቢኒያም የሚከተሉትን ጨምሮ ሰፊ ክሊኒካዊ እውቀት አላቸው፡
- የዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ
- የጉልበት መገጣጠሚያ ቅየራ
- የዳሌ ገንዳ እና የዳሌ ማቀፊያ ጉዳቶችን መቆጣጠር
- የዳሌ አጥንት አንገት እና የኢንተርትሮካንቴሪክ ስብራቶችን ማከም
- አጠቃላይ የእጅ እና የእግር ስብራቶች ሕክምና
እንደ ታንዛኒያ፣ ዛምቢያ እና ደቡብ ሱዳን ባሉ ሀገራት የAO Alliance የክልል ፋከልቲ አባል በመሆን ያገለገሉ ሲሆን በሱማሌላንድ በሚገኘው የሃርጌሳ ግሩፕ ሆስፒታል በቀዶ ህክምና ተልእኮዎች አዘውትረው አገልግለዋል።
በጥበብ ግዮን ሆስፒታል በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያውን ከፍተኛ የአጥንት አደጋ እና የአርትሮፕላስቲን ክፍል በማቋቋም የመጀመሪያው በአማራ ክልል በሕክምና የሰለጠኑ የአጥንት ህክምና ባለሙያ ናቸው። እንዲሁም በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ክፍል ኃላፊ እና የአደጋ ጊዜ አገልግሎት ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል።
ዶ/ር ቢኒያም የ2025 ኦቲኤ የሰብአዊ ስኮላርሺፕ (ዩኤስኤ) እና የ2025 ኢራስመስ+ KA171 የስታፍ ሞቢሊቲ ስኮላርሺፕ በስፔን ጨምሮ የተከበሩ አለም አቀፍ እውቅናዎች ተቀባይ ናቸው።
